ጠቅላላ

General

በአምላካችን አንጻር

Lyrics

በአምላካችን አንጻር እንዘምራለን

በእግዚአብሔር ቅዱሳን በግርማ ተከበን /2/

ሠማይ ተከፈተ ደስ ይበለን

ማሕሌት ተሰማ ደስ ይበለን

ዛሬ ተከበናል ደስ ይበለን

በመለኮት ግርማ ደስ ይበለን

በሰማይ ተሰማ የመላዕክት መዝሙር

የሠላም የደስታ የእውነት የፍቅር /2/

ደመና ከበበን ድንግል ተደሰተች

የሕዝቡን መመለስ ትመለከታለች /2/

ታላቅ ደስታ ነው በሰማይ ሠራዊት

ሰይጣን ድል ተነስቶ እኛ ስንባረክ /2/

ሰዎች እልል በሉ ውስጣችን ይታደስ

አምላክ ከእኛ ጋር ነው በልባችን ሊነግስ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening