✦
ጠቅላላ
•General
ፈተና ወጀብ ቢበዛ
Lyrics
ፈተና ወጀብ ቢበዛ አይተናል ህዝቡን ሲያበዛ
በሕይወት አንዴ ጠርቶናል እግዚአብሔር መች ይተወናል /2/
ፍቅር ነው የናርዶስ ሽቶ
ወደደን ተሰቅሎ ሞቶ
ነጎድጓድ መብረቅ ቢሆንም
በሕይወት አለን አሁንም /2/
መኳንንት ደጁን ክፈቱ
የጸጋው ፈልቷል ዘይቱ
ተራግፏል ሸክማችን
ምህረቱ ቢፈስልን /2/
ተጽናንቷል አርፏል ልባችን
በእሳት ታጥሯል ቅጥራችን
ብንወድቅም አንሸነፍም
ይዘናል የአምላካችን ስም /2/
ሕይወት ነህ የጽድቅ ጥላ
ያውቅሃል ቃል የተመላ
ነህ አንተ ጣፋጭ ምግባችን
እግዚአብሔር ቸሩ አምላካችን /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.