ጠቅላላ

General

ድንግል ትንሣኤሽን

Lyrics

ድንግል ትንሣኤሽን እስከምናይ ድረስ

ገብተናል ሱባኤ በአንድነት በመንፈስ

ለእኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት

አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነ ምህረት /2/

ሞትን የረገጠ ልጅሽ ካንቺ ጋር ነው

ውጦ የሚያስቀርሽ የቱ መቃብር ነው

የእርገትሽን ዜና ከቶማስ ሰምተናል

ትንሣኤሽ እውነት ነው ሰበንሽን አይተናል

ሞትማ በሞት ተሸንፏል በአንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል/2/

ልናየው ወደድን የቶማስን ክብር

ለምን ተሰወረን የትንሣኤሽ ምስጢር

በራችንን ዘግተን በጸሎት ወድቀናል

ተገልጠሽ አብሪልን ልጆችሽ ናፍቀናል

ሞትማ በሞት ተሸንፏል በአንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል/2/

መዝሙረኛ አባትሽ ዳዊት ጽፎልናል

ሞትን የማያይ ሰው ማን አለ ብሎናል

ይህ እውነት በዘመን አንቺ ላይ ቢደርስም

በሞት ተሸንፈሽ መቃብር አትወርጂም

ሞትማ በሞት ተሸንፏል በአንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል/2/

ቶማስ ከደመናው ወርዶ ሲያናግረን

ስለሆነው ነገር እጅጉን ተመስጥን

እኛም ይህን ክብር ተመኘን ለማየት

ድንግል አሳስቢልን ኪዳነ ምህረት

ሞትማ በሞት ተሸንፏል በአንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል/2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening