ጠቅላላ

General

የአብ ቃል አክብሮሽ

Lyrics

የአብ ቃል አክብሮሽ እናት ያደረገሽ

እግዚአብሔር በቃሉ ፍጹም ያከበረሽ

የምንመካብሽ መሰላል አንቺ ነሽ /2/

ቅድስና ለአንቺ ጽድቅም ለአንቺ ሆኖ

ዓለምን የፈጠረ በአንቺ ተወስኖ

የገነት ፍሬ ነሽ ሕይወትን ያፈራሽ

አንቺን ለመረጠ አንቺን ለአጸናሽ

ምስጋና ይድረሰው ለቸሩ አምላክሽ /2/

አዳም የኖረብሽ የኤዶም ገነት ነሽ

የኤፌሶን ወርቅ የሚፈልቅብሽ

የግዮን ማዕበል ኢትዮጵያን የከበብሽ

ዮርዳኖስ ሆነሽ አህዛብን ፈወስሽ

በልጁ ቃልነት አብም አከበረሽ /2/

መዓዛሽን ወዶ ወልድ ዋህድ ዋጀሽ

አብም በሰማያት በህሊናው ጻፈሽ

መንፈስ ቅዱስ መጥቶ አንቺን አከበረሽ

እመካብሻለሁ እመቤቴ ስልሽ /2/

ወልድ በመውደዱ ከአንቺ መወለዱን

ንጹህ ሆኖ አግኝቶሽ ቅዱሱን ስጋሽን

ለቃሉ ማደሪያው ጽላቱና ታቦት

በብሩህ ደመና ተመስለሽለት

ከስጋሽ ተከፍሎ ከደምሽ ደም ወሰዶ

ከነፍስሽም ነፍስ ፍጹም ተዋህዶ /4/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening