ጠቅላላ

General

የእቲሳ አንበሳ

Lyrics

የእቲሳ አንበሳ ተክልዬ ተነሳ

ወገንህን ታደገው ከሃጢያት አበሳ

ተኩላው ለምድ ለብሶ በእርግጥ መጥቷልና

ጴጥሮስ ሆይ ዝም አትበል እንደ ጥንቱ ቅና

ዮሐንስ ዝም አትበል እንደ ጥንቱ ቅና

የዓለም ምናምንቴ የተባልከው ቅዱስ

የዋሁ መነኩሴ አባ ሕርያቆስ

ቅዳሴ ማርያምን ናና ዛሬ ቀድስ

በዕጣኑ መዓዛ ድውያንን ፈውስ /2/

የወንጌል አንበሳ ጎርጎርዮስ ፍጠን

ምሶሶው ሳይወድቅ መንጋው ሳይበተን

መብረቁ አትናቴዎስ ሞገዱን ገስጸው

አፈ ጉባኤያችን በመስቀልህ ዳኘው /2/

መርከቧን የሚያውክ መብረቅ መጥቷልና

አምላካችን ፈጥነህ አድነን ቶሎ ና

ጴጥሮስ ሆይ ቀስቅሰው ልንጠፋ ነው ብለህ

ሞገዱ እያየለ ዝም እንዳይል ጌታ /2/

ከሳቴ ብርሃን ሰላማ ቶሎ ና

ኖላዊ እረኛ ያስፈልጋልና

ስጋውን የጎዳ ነፍሱን የጠቀመ

ነቅ ጉድፍ የሌለው ግብሩ የታረመ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening