ጠቅላላ

General

ገብርኤል ኃያል

Lyrics

ገብርኤል ኃያል መላከ ሰላም መላከ ብስራት

የምታወጣ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ከሚነድ እሳት

ፍቅርህ ተስሏል በልባችን

ፊትህ ቆመናል ባርከን ብለን

የጽናታቸው ዝናው ሲሰማ

ከዚያች ባቢሎን ከሞት ከተማ

ህፃናት ሳሉ በራ ዕምነታቸው

ቆመህ ተገኘህ መካከላቸው

ውሃው ሲዘልል ቢያስደነግጥም

በጋኖቹም ውስጥ ቢለዋወጥም

ጸንተው ዘመሩ ልጅና እናቱ

አንተ ስትደርስ ከዚያ ከእሳቱ

ቂርቆስም ጸና ሞትን ሳይፈራ

አንተ ሳላለህ ከነርሱ ጋራ

አትፍሪ አላት ስለምን ትፍራ

አምነው ድል ነሱት ያንን መከራ

እኔም አምናለሁ አድነኝ ብዬ

ቆመህ አማልደኝ ከቸር ጌታዬ

ክፉውን ዘመን የማልፍበት

ጽናትን ስጠኝ ድል ልንሳበት

እኔም አምናለሁ አድነኝ ብዬ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening