ጠቅላላ

General

ጽላት ዘሙሴ

Lyrics

ጽላት ዘሙሴ ዕፀጳጦስ ዘሲና /2/

ፀናጽል ፀናጽል /5/ ለአሮን ካህን

ኧኸ ኧኸ ፀናጽል /5/ ለአሮን ካህን

አልፌያለሁና እመቤቴ ያን ሁሉ መከራ

ከኔ ጋር ስለሆንሽ እመቤቴ ስምሽን ስጠራ /2/

በዚያ በጭንቅ ቀን ድንግል

እጅግ በሚያስፈራው ድንግል

ማን ያድነኝ ነበር ድንግል

ስምሽን ባልጠራ ድንግል

በሞትና ሕይወት ድንግል

መካከል ቢሆንም ድንግል

ታምርሽ አነሳኝ ድንግል

ማርያም አልተውሽኝም ድንግል አልተውሽኝም

እጅግ የከበደ ነበረ ያገኘኝ ፈተና

ታሪክ ሆኖ ቀረ እመቤቴ ባንቺ ዳንኩኝና /2/

ዙሪያው የሚያስፈራ ድንግል

ጽኑ ነው ገደሉ ድንግል

በዚያ የወደቁ ድንግል

እንዴት ይተርፋሉ ድንግል

ስምሽ ድጋፍ ሆኖ ድንግል

ከሥር ተነጠፈ ድንግል

በሚያስደንቅ ምስጢር ድንግል

ሕይወቴ ተረፈ ድንግል

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening