ጠቅላላ

General

ሰዎች ፈረዱብኝ

Lyrics

ሰዎች ፈረዱብኝ አንተ ግን አዳንከኝ /2/

አምላኬ ሆይ ተመስገንልኝ /2/

ሌላ ምን ቃል አለኝ

ሊያልፉኝ አልወደዱም ነቄን ሊሰውሩ

ሰዎች ፈጠኑብኝ በደሌን ሊያወሩ

አንተ ግን ሰብስበህ በፍቅር ሸፈንከኝ

በመተላለፌ አዝነህ ሳትለየኝ

ይህ ፍቅርህ ሰበረኝ አጣበቀኝ ከአንተ

ደጅህ ያወጣኛል ሁሌ እየጎተተ /2/

መርከሴን አውጀው ሲያነሱብኝ ድንጋይ

ሰወረኝ ታምርህ ልጅህ ሳልሰቃይ

ወደህ ስለማርከኝ ክፉዎች ተከዙ

ይህ አይደለም ብለው የኃጢአት ደሞዙ

ከአንተ በላይ ጌታ ማን ሊያውቀኝ ይችላል /2/

የፍቅርህን ሚዛን ማንስ ያዛባዋል /2/

ማዳንህ ይደንቃል ለወደኩት ልጅህ

ምህረትህ ይደፋል ሁሌም በሚዛንህ

እንደሰው አይታይ ፍርድህም ይለያል

ለባርያህ አርነት በምህረት ፈርደሃል

ፍቅር እየዘረዘርክ መንገዴን የጠረግህ /2/

ስለ ልጅህ ጽድቅን ለድህነት የፈረድክ /2/

እኔ አልፈርድብህም በሰላም ሂድ አልከኝ

ዳግም እንዳልበድል በፍቅር እያየኸኝ

ወደ ጽድቅህ ህጎች ነፍሴን አፈሳለሁ

እንዲህ ከወደድከኝ ወዴት እሄዳለሁ

አልለይም ካንተ ከፍቅር መድረኬ /2/

አመልካለሁ አንተን ፊትህ ተንበርክኬ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening