ጠቅላላ

General

ኪዳነ ምህረት እናቴ

Lyrics

ኪዳነ ምህረት እናቴ አማልጅኝ እኔን ከልጅሽ

የፍቅር እናት ነሽና አማልጅኝ እኔን ከልጅሽ

የሰላም እናት ነሽና አማልጅኝ እኔን ከልጅሽ

የተገለጠው ብርሃን ከምስራቅ የተወለደው

በፍቅር ሰንሰለት አስሮ ዓለምን ሁሉ አዳነው /2/

እንደው ዝም ብሎ ይገርመኛል የአምላክን ሥራ ሳስበው

ምክንያት አንቺን አድርጎ ይህንን ዓለም አዳነው /2/

በረሃውን ባሰብኩት ጊዜ የግብጽን አሸዋ ግለት

አንቺ ትንሽ ብላቴና ኧረ እንዴት ቻልሽው በእውነት /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening