✦
ጠቅላላ
•General
እንዲህ እናምናለን
Lyrics
እንዲህ እናምናለን እንታመናለን /2/
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ እግዚአብሔር ብለን /2/
የእግዚአብሔር አብ ፍቅሩ ይሰፋል ይረቃል
ልጁን እስኪሰጠን እንዲሁ ወዶናል
በደብረ ታቦር ላይ እርሱን ስሙት ላለው /2/
በመዝሙር ለቃኘን ምስጋና ይድረሰው /2/
አብርሃም ይስሃቅን አባት እንደሆነው
አይደለም ልደቱ በአማን ልዩ ነው
የተወለደ ነው ከቶ አልተፈጠረም /2/
ከአባቱ ጋር ቅድመ ዓለም የኖረ /2/
ሊያጽናናን የሚላክ ከአብ የሚወጣ
በሃምሳኛው ዕለት ወደ እኛ የመጣ
የራሱ የሆነ ፍጹም አካል ያለው /2/
ጰራቅሊጦስ ጌታ እግዚአብሔር አምላክ /ቅዱስ/ ነው/2/
በዕደ ዮሐንስ ሲጠመቅ በማይ
ወልድ አምላክ መሆኑን ስንሰማ ከላይ
በአምሳለ እርግብ ወርዶ በርሱ የኖረው /2/
አካላዊው ቃል እስትንፋስ ሕይወት ነው /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.