ጠቅላላ

General

ኢትዮጵያዊው ጻድቅ

Lyrics

ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ማነው ብዬ ጠየኩ

በረከት ፈልጌ ልሳለመው ናፈኩ

ክብሩን ልመሰክር ተፈታ ምላሴ

ከደጁ ደርሼ ፍቅሩን በመቅመሴ

በእቲሳ ምድር ዘር ሆነህ በቅለህ

ተለየህ ለአምላክ ዓለምን ጥለህ

ደብረ ሊባኖስ ህያው ምስክር

ስለ አንተ ዝና ስለ አንተ ክብር

ተ/ሃይማኖት ወዳጄ ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ

አክባሪው አምላክ ስላከበረህ

ዛሬም ከእኛ ጋር በመንፈስ አለህ

ደጅ እንጠናለን በትህትና

የጻድቅ ጸሎት ሃይል አላትና

ተ/ሃይማኖት ፀሐይ ጸጋህ ይምጣልኝ ከሰማይ

ወደ ለምለም መስክ ሰብከህ መራኸን

የቃሉን ወተት አጠጥተኸን

ያቀጣጠልከው የወንጌል ችቦ

የአምላክ አድርጓል ትውልዱን ስቦ

ተ/ሃይማኖት ወዳጄ ተባርኳል በአንተ ቤቴ ደጄ

ሰላሳ ስልሳ መቶ ያፈራሕ

በደብረ አስቦ ቆመህ በአንድ እግርህ

የመቶ ሎሚ መሻት ቀረና

የጌታ መንገድ ጥርጊያውም ቀና

ተ/ሃይማኖት ወዳጄ ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening