ጠቅላላ

General

ባርከን ባርከን

Lyrics

ባርከን ባርከን ልጆችህን ባርከን /2/ ኧኸ

ቅዱስ መንፈስህ አንድ ሃሳብ አድርገን /2/

ባርኪን ባርኪን ልጆችሽን ባርኪን

ድንግል ሆይ በምልጃሽ አንድ ሃሳብ አድርጊን /2/

ድንግል ሆይ በምልጃሽ ከልጅሽ አስታርቂን /2/

ጥሪህን ስንሰማ ወደ አንተ እንድንመጣ

በሕግህ ልንኖር ከቤትህ ላንወጣ

በሕይወት ስንደክም እንዳንጠፋ በዓለም

እርዳን ፈጣሪያችን ቸሩ መድኃኒዓለም

ባርከን ባርከን

ተፈረደብን የባርነት ሕይወት

መጣብን መርገም በመብል ምክንያት

ሲኦል እስራት እኛ የዳንብሽ

ድንግል ሆይ ምንጊዜም አይለየን ምልጃሽ

ባርኪን ባርኪን

አንድነት ስናጣ ፍቅር ስትመነምን

በምግባር ስንደክም ሲጎል እምነታችን

በስጋችን ፈቃድ ወደን እንዳንጠፋ

በምህረትህ ጎብኘን አንተ ሁነን ተስፋ

ባርከን ባርከን

ንጽህተ ሕሊና ቅድስት እናታችን

አሳስቢ ሁልጊዜ ስለ ሃጢአታችን

ሊያድነን ነው እና ክርስቶስ በሞቱ

አስምሪን እማምላክ ድንግል ወላዲቱ

ባርኪን ባርኪን

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening