ጠቅላላ

General

የአፎሚያ ረዳት

Lyrics

የአፎሚያ እረዳት ነህ ሚካኤል /2/

ቅሩበ እግዚአብሔር የልዑል

ፈጥነህ ድረስልን ስንጠራህ ሚካኤል

ፊት ለፊታችን አምላክ ሰደደህ

አቀናህልን መንገዱን ጠርገህ

የቤሊሆርን ምክር እያፈረስክ

ከልጆችህ ጋር ከነዓን ደረስክ

ከእኛ ጋር ነበርክ አርባውን ዘመን

እንጠራሃለን ሚካኤል ብለን

በቃዴስ ክንፍህ ተዘርግቶልን

ደመናው ባንተ ተጋረደልን

አብረኸን ልትሆን ጌታ የላከህ

አንተ ሚካኤል ታዳጊያችን ነህ

ሙሴ ሲለየን ደጉ አባታችን

ሚካኤል ነበርክ ከላይ መሪያችን

የባርነቱ ጉዞ እስኪያበቃ

እጅግ ረዳት የእኛ ጠበቃ

ሳጥናኤል መክሮን የሐሰት ምክር

ሊወስደን ሻተ ሙሴ መቃብር

ስለማይጠቅመን አንተ ሰወርከው

ምክሩን በታትነህ አስጎነበስከው

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening