ጠቅላላ
•General
የሰላምታሽን ድምፅ
የሰላምታሽን ድምፅ ስሰማ እመቤቴ /2/
ሀዘኑ ጠፋልኝ በዛልኝ ሐሴቴ /2/
የሰላምታሽን ድምፅ ከተራራው ሀገር
የሰላምታሽን ድምፅ ከኤፍሬም ከተማ
የሰላምታሽን ድምፅ ልቤ ተረጋጋ ድምፅሽን ሲሰማ
የሰላምታሽን ድምፅ ቅድስት ኤልሣቤጥ ሆይ
የሰላምታሽን ድምፅ በጣሙን ታደልሽ
የሰላምታሽን ድምፅ የአምላኬን እናት አጽናኝ አገኘሽ
የሰላምታሽን ድምፅ ተገብቶኝ አይደለም
የሰላምታሽን ድምፅ ቃልዋን ለመስማት
የሰላምታሽን ድምፅ ፈቃዷ ሆነና ተሞላው ሐሴት
የሰላምታሽን ድምፅ አንተ የእግዚአብሔር ካህን
የሰላምታሽን ድምፅ በደህና ሂድ በለኝ
የሰላምታሽን ድምፅ የእመቤቴ ድምጿ ስንቅ እንዲሆነኝ
የሰላምታሽን ድምፅ ነጎድጓድ ነው ቃሏ
የሰላምታሽን ድምፅ እኔን ያጽናናኝ
የሰላምታሽን ድምፅ ቤተ መቅደስ ሆዷ ነው የሰማ
የሰላምታሽን ድምፅ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ
የሰላምታሽን ድምፅ ይኸው ተሞላሁኝ
የሰላምታሽን ድምፅ ምስጋና ለድንግል ለማቅረብ በቃሁኝ
የሰላምታሽ ድምፅ በቅዳሴው መሃል
የሰላምታሽ ድምፅ ውብ ቃልሽ ይሰማል
የሰላምታሽ ድምፅ ሁሉም ተረጋግቶ አንቺን ያዳምጣል
የሰላምታሽ ድምፅ ያዘነ ያጽናናል
የሰላምታሽ ድምፅ ትካዜን ያጠፋል
የሰላምታሽ ድምፅ ድንግልን የሰማ በተድላ ይኖራል
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.