✦
ጠቅላላ
•General
ተነሳልን
Lyrics
ተነሣልን መድኃኒታችን /2/
ከዲያቢሎስ ግዞት ነጻ ሊያወጣን
በመስቀል ተሰቅሎ ባፈሰሰው ደም
ተደመሰሰልን የሃጢአት መርገም
በጠንካራ ድንጋይ መቃብር ቢዘጋ /2/
ድል አድርጎ ተነሳ አልፋና ኦሜጋ /2/
ሞትን ድል አድርጎ ለተነሳው አምላክ
እኛን ከባርነት ለታደገን በእውነት
ጌታዬ ተመስገን ሌላ ምን እላለሁ /2/
ለከበረው ስምህ ምስጋና አቀርባለሁ /2/
እልልታን እናቅርብ ለሃያሉ ንጉሥ
ሞትን አጠፋልን እኛን ለመቀደስ
ከባርነት ቀንበር እኛን አላቆናል /2/
በመስቀል ተሰቅሎ ሕይወቱን ሰጥቶናል /2/
የአዳም ልጆች ሁሉ እንዘምር በእልልታ
ለሃያሉ እግዚአብሔር ለሰራዊት ጌታ
እንዘምር ዘምሩ ሰዎች ደስ ይበለን /2/
ሞትን አሳፍሮ ጌታ ተነሳልን /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.