✦
ጠቅላላ
•General
በንጹህ ደሙ
Lyrics
በንጹህ ደሙ ያዳነን
ከወደቅንበት ያነሳን /2/
ብዙ ነው የእርሱ ውለታ
እንዘምራለን ለጌታ
ቀና ብለናል በክብረ
አንገቱን ደፍቶ በፍቅር
ስለኛ ብዙ ሆኖልን
የብርሃን አክሊል ደፋልን
የዓለም መድሃኒት ጌታ ነው
ጠላታችንን ያሰረው /2/
እርቃኑን ሆኖ ሸለመን
እየደከመ አቆመን
እርሱ በመስቀል ሲሞት
እኛ ተፃፍን በሕይወት
የዓለም መድሃኒት ጌታ ነው
ጠላታችንን ያሰረው /2/
እስከ ሺ ትውልድ ይምራል
ፍቅር ነውና ይራራል
አይዝልም የእርሱ ትከሻ
መጨረሻ ነው መድረሻ
የዓለም መድሃኒት ጌታ ነው
ጠላታችንን ያሰረው /2/
በደም ያጌጠ ልብስ አለው
ከአማልክት ማንም አይመስለው
ትውልዱ ማዳኑን ይስማ
ነግሷል በፅዮን ከተማ
የዓለም መድሃኒት ጌታ ነው
ጠላታችንን ያሰረው /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.