✦
ጠቅላላ
•General
እረድተሃልና
Lyrics
እረድተሃልና ባህራንን ሚካኤል
ጠብቀሃልና ቴዎብስታን ሚካኤል
አስታርቀን አማልደን ሚካኤል
ከሰማያት ስትወረድ ሚካኤል
ለሰው ልጆች ልትራራ ሚካኤል
በክብርህ የተነሳ ሚካኤል
መላው ምድር አበራ ሚካኤል
በመከራዬ ጊዜ ሚካኤል
ፈጥነህ የደረስክልኝ ሚካኤል
ከአምላኬ ተልከህ ሚካኤል
ከጭንቅ የገላገልከኝ ሚካኤል
አልተረዳሁትም ሚካኤል
በእጄ ያለውን ሚካኤል
የሞቴን ደብዳቤ ሚካኤል
የሸሸኩትን ሚካኤል
ልጨብጥ ስጣደፍ ሚካኤል
የሰይፉን ስለት ሚካኤል
የመላዕክት አለቃ ሚካኤል
አዳነኝ ከሞት ሚካኤል
ገና ህፃን ሳለሁ ሚካኤል
አሳድገኸኛል ሚካኤል
ከብዙ ፈተና ሚካኤል
አንተ አድነኸኛል ሚካኤል
አሁንም ጠብቀኝ ሚካኤል
ቸል አትበለኝ ሚካኤል
አባቴ ሚካኤል ሚካኤል
ልጄ ሆይ በለኝ ሚካኤል
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.