ጠቅላላ

General

ንቁም

Lyrics

ንቁም በበሕላዊነ /4/

እስከ ንረክቦ ለመላዕክነ

ገብርኤል አለ ለመላዕክቱ

ጸንተው በመቆም እንዲበረቱ

እንደ ሊባኖስ ዝግባ ከፍ ያሉ

የጥፋት ልጆች ምድርን ቢሞሉ

አብዝተን እንጩህ ስሙን እንጥራ

እንጠብቅ ጌታን ለእኛ እስኪራራ

ሐሰት ቢነግስም እውነት ተረግጦ

ቃየል ሲነሳ ድንጋይ ጨብጦ

ጸብ ክርክሩ ቢያነዋውጸን

እንቁም በእምነት ትዕግስትን ይዘን

ብርቱ ሰንሰለት በእኛ ላይ ቢከብድ

በእሾህ ቢታጠር መሄጃው መንገድ

አይናችን ቢያይም ሰላም ደፍርሶ

መርዙን ይነቅላል እግዚአብሔር ደርሶ

መናወጥ ቢሆን በመርከባችን

ሞት ቢያጠላባት ጓዳ ደጃችን

ግራ ቀኝ ሳንል ፍጹም እንጽና

እግዚአብሔር እስርን ይፈታልና

ደስታችን ሲርቅ ላንደርስበት

ፊታችን ቢርስ በእንባ ጅረት

የሚያረጋጋን በሃያል ቃሉ

እግዚአብሔር አለ ያልፋል ይህ ሁሉ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening