ጠቅላላ
•General
ምህረት ከአምላክህ
ገና ሕጻን ሳለህ ጌታ መርጦሃል
ተክለሃይማኖት ክብር ይገባሃል
ኢትዮጵያ ሀገርህን አትተዋት
ምህረት ከአምላክህ ለምንላት
አንተ የደከምክበት ተ/ሃይማኖት አውሬው ሰልጥኖብን ተ/ሃይማኖት
ያ መልካም አዝመራ ተ/ሃይማኖት ተፍገምግመናል ተ/ሃይማኖት
እንክርዳድ ሞላበት ተ/ሃይማኖት ተክልዬ አትተወን ተ/ሃይማኖት
ተክለ አብ ቶሎና ተ/ሃይማኖት ከአምላክ አስታርቀን ተ/ሃይማኖት
የምንኩስናውን ተ/ሃይማኖት ዛሬ በእኛ ጊዜ ተ/ሃይማኖት
ተግባሩን የፈጸምክ ተ/ሃይማኖት ክደቱ በርትቷል ተ/ሃይማኖት
ጣኦታትን ሰብረህ ተ/ሃይማኖት መንጋ የሚጠብቅ ተ/ሃይማኖት
ጠላትን ያሳፈርክ ተ/ሃይማኖት አባት ያስፈልጋል ተ/ሃይማኖት
ገድላት ታምራቷን ተ/ሃይማኖት ለአንዲቱ ሃይማኖት ተ/ሃይማኖት
ንቀው ሲያቃልሉ ተ/ሃይማኖት ለቀደመቺቱ ተ/ሃይማኖት
ስርዓቷን ጥሰው ተ/ሃይማኖት መከታ ሁንላት ተ/ሃይማኖት
እናድሳት ሲሉ ተ/ሃይማኖት ዛሬም እንደ ጥንቱ ተ/ሃይማኖት
ተኩላ ቤቱ ገብቶ ተ/ሃይማኖት ዘመኑን ምሰሉ ተ/ሃይማኖት
ከበጎች መሃል ተ/ሃይማኖት እያለ ሲያባብል ተ/ሃይማኖት
ክህደትን ሲያስተምር ተ/ሃይማኖት ቶሎ ድረስልን ተ/ሃይማኖት
ሕዝቡን ሲያታልል ተ/ሃይማኖት አንተ ዝም አትበለን ተ/ሃይማኖት
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.