ጠቅላላ

General

ፃድቃን ሰማዕታት

Lyrics

ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ

በአካለ ስጋና በአካለ ነፍስ /2/ ያሉ

ከፈጣሪ አማልደው እኛን ያስምራሉ

የእግዚአብሔር አይኖቹ ጻድቃን ከማየት

ጆሮቹም አይርቁም እነርሱን ከመስማት

የጻድቅ ሰው ጸሎት ሃይልን ታደርጋለች

በምልጃቸው ድነን

የእግዚአብሔር መከራ ሳያሳቅቃቸው

እሳትና ስለት ሳያስፈራራቸው

ሰማያዊ ተስፋ ስለሚታያቸው

በፈተና ሁሉ ጸኑ በእምነታቸው

ሃጥኡ ነዌ እንኳን በሲኦል እያለ

ስለ ወንድሞቹ ምህረት ከለመነ

እናንተማ ጻድቃን በገነት ያላችሁ

ምንኛ ትረዱን አምነን ስንጠራችሁ

ቀዝቃዛ ውሃ እንኳን በጻድቅ ሰው ስም

የሚያጠጣ ቢኖር ዋጋው አይጠፋም

ብሎ እንዳስተማረ ጌታ በወንጌል

አምነን እንፈጽመው ዋጋ ያሰጣል

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening