✦
ጠቅላላ
•General
ቤተ ክርስቲያን
Lyrics
ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት /4/
አትመረመርም /2/ እጅግ ጥልቅ ናት
ኧኸ አትመረመርም /2/ እጅግ ጥልቅ ናት
በስጋዊ ጥበብ ለማወቅ ቢቃጣ /2/
የዕምነት መነጽሩን ይዞ ስላልመጣ /2/
አንዳንዱ በክህደት /2/ ፈጣሪውን አጣ
ኧኸ አንዳንዱ በክህደት /2/ ፈጣሪውን አጣ
የመስቀሉ ቃል ለእኛ የእግዚአብሔር ሃይል ነው /4/
ለማያምኑት ሞኝነት ነው ለእኛ ግን ሕይወት ነው
ኧኸ ለማያምኑት ሞኝነት ነው ለእኛ ግን ሕይወት ነው
እንመሰክራለን ፈጣሪያችን አለ /2/
እንመሰክራለን አማኑኤል አለ /2/
አንዳንዱ ቢክደው /2/ እየተታለለ
ኧኸ አንዳንዱ ቢክደው /2/ እየተታለለ
እንመሰክራለን ማርያም አማላጅ ናት /2/
እንመሰክራለን ድንግል አማላጅ ናት /2/
ወላዲተ አምላክ /2/ መሰረተ ሕይወት
ኧኸ ወላዲተ አምላክ /2/ መሰረተ ሕይወት
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.