ጠቅላላ

General

ማርያም

Lyrics

ማርያም /3/ ደስ ይበልሽ በገብርኤል ሰላምታ

ባንቺ ስላደረ የዓለሙ ሁሉ ጌታ /2/

የአምላክ ቸርነቱ ፈቃዱ ሲሆን

ጨለማው ተገፎ ሲወጣ ብርሃን

መድሃኒት ሲመጣ ሰይጣን እንዳፈረ

የዜናው አብሳሪ ገብርኤል ነበረ

ገብርኤል /2/ ዜናዊ ሐዲስ

የአምላክን መወለድ ስጋን በመልበስ

በቤተ መቅደስ ተቀምጣ ድንግል

ሐርና ወርቁን አስማምታ ስትፈትል

ገብርኤል ሲያበስራት ድንግል ስትሰማ

በእርሷ ላይ አደረ የመለኮት ግርማ

እውነተኛ መልአክ መሆኑን ስላየች

ይሁንልኝ ብላ ቃሉን ተቀበለች

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening