✦
ጠቅላላ
•General
ይላል አንደበቴ
Lyrics
ይላል አንደበቴ እግዚአብሔር ቅዱስ ነው
አይተወኝምና ወላጅ እንደሌለው
ትላንት የጠበቀኝ የነገም ተስፋዬ
ትላለች ነፍሴ ፍቅር ነህ ጌታዬ
የትላንት ሕይወቴን ዞር ብዬ ሳየው
ማምለጫ የሌለው አጥሩም እሾህ ነው
ወደርስቴ ወጣሁ ይድረስ ምስጋናዬ
ደጆች ቢዘጉብኝ በር ሆኖኝ ጌታዬ/2/
በጥልቁ በረሃ ምግብ መጠጥ ሆኖኝ
መንገዴን አቀና እጄን በአፌ አስጫነኝ
በእሳትና ውሃ መካከል አልፌ
ተመስገን እላለሁ ቅኔ ሞልቶት አፌ/2/
የብቸኝነቴን መዐበል ገስጿል
ለኔ ብርሃን ሆኖ ለከሳሽ ጨልሟል
ቀስቱን እያለፈ ታደገኝ ከስቃይ
የጌታዬ ሃሳብ ፍቅር ነው በኔ ላይ /2/
ትላንት ዛሬ ነገ ዘላለም ጠባቂ
የልቤን ፍላጎት ሳልነግርው አዋቂ
በባህሪው ቅዱስ የሌለው አምሳያ
ስሙ መደቤ ነው መልህቄን መጣያ/2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.