ጠቅላላ

General

ድንግል ማርያም

Lyrics

ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ አሰምታ ትናገር ነበር

ሰላም ላንቺ ይሄን አለኝ ቅዱስ ገብርኤል

ሌላ ምንም አላውቅ ያውቃል እግዚአብሔር /2/

ከመቅደስ ቁኝ ብዬ ትንቢት እየሰማሁ

ሀሩን አስማምቼ ጥበብን እየፈተልኩ

ሳለሁ በመገረም ያንን ቃል አስቤ

አምላክ ሰው ሆነብኝ ተመሰጠ ልቤ

ማናት ብዬ ሳስብ ያቺ ብላቴና

ገብርኤል ደረሰ ብስራቱን ያዘና

ዙፋኑ አደረገኝ የባሪያቱን ውርደት ተመልክቷልና

እንዴት ያንን ማህፀን ሰማይን ይሆናል

የልዑሉ ዙፋን ወዴት ይተከላል

እያልኩኝ ስጠይቅ በልቤ ለራሴ

የመንፈስ ቅዱስ ሃይል አደረ በራሴ

ማናት ብዬ …….

እንዴት ከድሃ ቤት ይሄ ንጉስ ያድራል

ለርሱ የተገባ ሰው ወዴት ይገኛል

ገሊላን አሰብኳት ዞሬ በህሊና

ለካስ ተሸንፏል በባሪያው ትትና

ማናት ብዬ ……

እሳት የማይበላው ሀመልማል አይኖርም

እንዲህ ያለ ቅጠል ናዝሬት አይገኝም

ህሊናዬ መጥቆ ሲበር ወደ ሲና

አንቺኮነሽ አለኝ ገብርኤል መጣና

ማናት ብዬ …….

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening