✦
ጠቅላላ
•General
አጌጥንበት
Lyrics
አጌጥንበት ስምህን ተዋብንበት ፍቅርህን
ሞገሳችን ሆነሃል የጽድቅ ልብሳችን አማኑኤል /2/
ተዋህዶ የአዳምን ስጋ አማኑኤል ሆነ ከኛጋ
በግርግም በቤተልሔም ተወልዶ ሆነልን ሰላም
ብንጠግብ በልተን ጠጥተን ብንገባ በሰላም ወጥተን
ልጆችን ወልደንም ብንስም ጠርተን ነው ጌታ ያንተን ስም
ቢያምርብን ቢሞቀን ለብሰን ብንረሳ ለቅሶና ሀዘን
ፍቅርህ ነው ዛሬን ያሳየን ተመስገን እንልሃለን
በባእድ ሀገር ብንኖር ቢገጥመን መከራ ችግር
ነጩን ልብስ ለብሰን ታይተናል መስቀሉን ከማህተቡ ጋር /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.