ጠቅላላ

General

መርዓዊ ሰማያዊ

Lyrics

መርዓዊ ሰማያዊ /2/

ለእመ ገብረ በዓለ /2/አኸ /2/

ይኑሩ በሰላም /3/ ፀንተው ዘለዓለም

ደናግል ተነሱ ያዙ መብራትን

ሙሽራው ደረሰ አጉል እንዳንሆን

ወንጌልን ይዘዋል ጎዳናቸው ያምራል

ዓላማው መልካም ነው እነሱን እንምሰል

የድካም ዋጋቸው /2/

ብርሃኑ ያበራል በሃይማኖታቸው

የሙሽራው ሕይወት መልካም እንዲሆን

ካህኑ ይባርኩት ብሩክ ሰው ይሁን

የሙሽሪት ሕይወት መልካም እንዲሆን

ካህኑ ይባርኳት ብሩክት ትሁን

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening