✦
ጠቅላላ
•General
እልል እልል
Lyrics
እልል እልል ደስ ይበለን /2/
አጅበን መጣን ሙሽሮችን
እልል ብላችሁ ተቀበሉን
እናንት ሙሽሮች እንኳን ደስ አላችሁ /2/
የአብርሃም የሣራ ይሁን ጋብቻችሁ
መልካም መተሳሰብ ክርስቶስ ይስጣችሁ
ሣራና አብርሃም ሁሉም የሚያውቃቸው
ሁለቱም ቅዱሳኖች ናቸው
ፍቅራቸውን አይቶ አምላክ ባረካቸው
ለእናት ለአባት ታዛዥ ብሩክ ልጅ ሰጣቸው
ለጌታ መስዋዕት እኔ ልቅረብ ያለው
ይስሐቅን ለአብርሃም የሰጠው
በመልካም ጋብቻ በጥሩ ትዳር ነው /2/
ቅዱስ አባታችን ፈጣሪያችን ሆይ
ጌታችን አምላካችን ሆይ
በአብርሃም ጎጆ እንደገባህበት
በሙሽሮችም ቤት በረከት ሙላበት /2/
በቃናዋ መንደር የተዳርክ ሰርገኛ /2/
አምላክ ተገኘልህ ሆነህ እድለኛ /2/
በቃናዋ መንደር የተዳርሽ ሠርገኛ
ድንግል ጎበኘችሽ ሆነሽ እድለኛ
ማርያም ጎበኘችሽ ሆነሽ እድለኛ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.