✦
ጠቅላላ
•General
የቃናው ደስታ
Lyrics
የቃናው ደስታ ዛሬ ተደገመ
ጌታ ከእናቱ ጋር በሠርጉ ታደመ
የዘለዓለም አምላክ ስለአለ በዚህ ቤት
ሙሽራው ሙሽሪት አጉኙ በረከት
መርዓት ተሸልማ የድንግልና አክሊል
እዩት ሥርዓቱን እጅግ ያስደስታል
አንድ አካል ሙሽሮች እዩአቸው ሲአበሩ
በወንጌሉ በተክሊሉ ሄዱ እየተመሩ
እንግዳችሁ ብዙ ድንኳናችሁ ሙሉ
ጌታ ከእናቱ ጋር አለ በመሃሉ
የወይን ጋኖቹ ዛሬ ሙሉ ናቸው
አማኑኤል ድንግል ማርያም ስለአሉ ቤታቸው
በክብር ታጅቦ ሲመጣ መርዓዊ
እጅግ ያስደስታል አይደለም ምድራዊ
ዛሬ በዚህ ድንኳን ደስታ ተደረገ
በአማኑኤል በአምላካችን ስለተባረከ
በተክሊል በቁርባን የሆነው አንድነት
አይነጣጠልም ዳግም ወደ ሁለት
ሙሽሪት ሙሽራ ተደሰቱ ዛሬ
በሠርጋችሁ ተገለጠ የእምነታችሁ ፍሬ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.