ጠቅላላ

General

ሁለቱም አንድ ሆኑ

Lyrics

ሁለቱም አንድ ሆኑ ዛሬ /2/

በእግዚአብሔር በሕያው ቃሉ

ሁለቱም አንድ ሆኑ ዛሬ

ወንድና ሴት አደርጎ የፈጠራቸው

በሁዋላም በቃሉ አንድ አደረጋቸው

እናትና አባቱን የአዳም ልጅ ይተዋል

ከሚስቱም ጋር በሰላም በአንድ ይተባበራል

ሁለቱ አንድ ሥጋ ሆነው ይኖራሉ

ብሎ አስተምሮናል ጌታችን በቃሉ

አንድ ሥጋ ናቸው አይደሉም ሁለት

የባልና የሚስት ሕይወት ውሕደት

እንግዲህ እግዚአብሔር ካጣመራችሁ

በሆነው ባልሆነው ሰው አይለያችሁ

ለወገኖቻችሁ ምሳሌ ሆናችሁ

በክርስቶስ ፍቅር አምላክ ያቁማችሁ

ምንጣፋችሁ ንጹሕ መኝታችሁ ቡሩክ

ስለሆነላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ

ዓለም እንዲደነቅ ጠላት አንዲያፍር

በሃዘን በደስታ ይኑራችሁ ፍቅር

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening