✦
ጠቅላላ
•General
ደመቀ አበራልን
Lyrics
ደመቀ አበራልን የአማኑኤል ሥራ /2/
ሙሽሮቹ ሆኑ አብርሃም ወሣራ
በቤተ ክርስቲያን ጥላ ተጠልለው
ተክሊል አድርገዋል ሙሽሪት ሙሽራው
ፀጋ መንፈስ ቅዱስ ስለተሰጣቸው
ሙሽሪት ሙሽራው አበራ ገጻቸው
የተራራቀ አካል አንድ ሆነ በተክሊል
እግዚአብሔር ይመስገን እልል እልል እንበል
አጥንትሽ ከአጥንቴ ሥጋሽ ከሥጋዬ
አዳም የሰበከው ይኸው ዛሬ ታዬ
የተክሊክ ብርሃንዋ በእኛ መሃል በርቶ
እረቂቅ አንድነት ታየ በእርስዋ ጎልቶ
ይህን ድንቅ ነገር ለማየት ያበቃን
ሚስጥሩን የሚገልጥ እግዚአብሔር ይመስገን
ነጭ መጎናጸፊያ በአንድ ተጎናጽፈው
በመንፈስ ቅዱስ ሃይል አረፉ ከጥላው
ሙሽሪት ሙሽራው ለፍቅር ተሸነፉ
ለቁርባን መቁረቢያ ነጭ ልብስ አሰፉ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.