ጠቅላላ

General

ሙሽራዬ

Lyrics

ሙሽራዬ /3/ አበባዬ

ከጎንህ የምትሆን እህት አገኘህ

የእኛማ ሙሽራ እንኳን ደስ አለህ

በእግዚአብሔር ፈቃድ ለዚሁ ከአበቃችሁ

ቤታችሁ ይመረቅ በፍቅር ያጽናችሁ

ወንድ አግኝተሻል የሚያስብልሽ

የእኛማ ሙሽራ እንካን ደስ አለሽ

እግዚአብሔር ይመስገን እኛም ደስ ብሎናል

በቤተ ክርስቲያን ሠርጋችሁ ውብ ሆኗል

እንደነፍስህ አድርገህ እንድትወዳት

አደራ ሰጠንህ በጌታችን ፊት

እንድታስቢለት አንቺም ለአካልሽ

አደራ ትላለች ወንጌል እናትሽ

በሥጋ በደሙ ሕይወት አግኝታችሁ

ፍሬአችሁም ይብዛ ይባረክ ጓዳችሁ

አምላክ ያለበት ነው ይኼ ጋብቻችሁ

እስከ መጨረሻው ኑሩ ደስ ብሏችሁ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening