✦
ጠቅላላ
•General
ሙሽሮች አበበ ፍሬአችሁ
Lyrics
ሙሽሮች አበበ ፍሬአችሁ /2
ለዚህች ቀን ይኸው ደረሳችሁ
በአምላክ ፊት እጅግ ከበራችሁ /2/
በእግዚአብሔር ቸርነት በመልካም ፈቃዱ
በቅዱስ ቁርባኑ ዛሬ ተዋሐዱ /2/
በሥርዓተ ተክሊል በሥጋ ወደሙ
በመድሃኔዓለም ፊት ጋብቻን ፈጸሙ /2/
በቤተክርስቲያን በፈጣሪአቸው ፊት
ሁለቱም አንድ ሆኑ በዚህች ቅድስት ዕለት /2/
አንድ የሚያደርጋቸው ተነቦ ወንጌሉ
በካህኑ መስቀል በረከት ታደሉ /2/
በወንጌል ብርሃን በሐዋርያት ቃል
በእመብርሃን ፊት ጋብቻችሁ ሰምሯል /2/
በአምላክ ሥጋና ደም ሁለቱም ታተሙ
የሕብረት ቃል ኪዳን በአንድ ላይ አሰሙ/2/
ጸንቶ የሚያጸድቅ የማይለያያቸው
ክቡር ቃል ስለአለ በመካከላቸው /2/
እስከ መጨረሻው አንድ አካል ሆነዋል
የአማኑኤል ሥጋ አስተሳስሮአቸዋል /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.