✦
ጠቅላላ
•General
በሠርጋችን ዕለት
Lyrics
በሠርጋችን ዕለት እንድትባርከን
ጌታ ጠርተንሃል በዕምነት ሆነን
ከእናትህ ጋር ከእመቤታችን
ከመላእክትህ ጋር ና በሠርጋችን
ከሐዋርያት ጋር ና በሠርጋችን
ከወዳጆችህ ጋር ና በሠርጋችን
በገሊላ መንደር እንደተገኘህ
ና በእኛ ድንኳንም ጌታ ስንጠራህ
የጥሪ ወረቀት ልከናል እንዳትቀር
አንተ ነህ ክብራችን የቤታችን ፍቅር
ነይ ከልጅሽ ጋር እመቤታችን
እንድታሟይልን የጎደለውን
ንገሪው ለልጅሽ ባዶውን እንዲሞላ
በረከት የእርሱ ነው ቤታችንን ይሙላ
በጎደለው ሁሉ እየጨመርሽልን
ቤታችንን ሁሉ ሙይው እናታችን
ለአገልጋዮችም ድንግል ንገሪያቸው
ጠርተን እንዳናፍር ጋኖችን ይሙሉአቸው
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.