ጠቅላላ

General

አጅቡት በእልልታ

Lyrics

አጅቡት በእልልታ ሲመጣ ሙሽራው

ፍጹም የሚያስደስት የሠርጉ ዕለት ነው

ዘመዶቹ ሁሉ ተቀበሉት ውጡ

የሙሽራው መምጫ አሁን ነው ሰዓቱ

እልል /2/ እንበል እንዘምር በደስታ

ይህን ለአደረገ ለሠራዊት ጌታ

ሁሉንም በጊዜው ይፈጽማልና

ይኸው አበቃቸው ለዚህ መልካም ዜና

ሙሽሪት ተደሰች ዝምታው ምንድነው

የዳግም ልደትሽ የሠርግሽ ዕለት ነው

አዳም ጎንሽ ቆሞ ሔዋን ሆይ ሲልሽ

መንፈሳዊ ሐሴት ይሙላ በልብሽ

እህት ወንድሞቿ እናትና አባትዋ

ተነሱ ዘምሩ ለልጃችሁ ደስታ

መሄድዋ ነውና ወደ ቤቷ ዛሬ

ወደ አዲስ ጎጆዋ ሸኟት በዝማሬ

ቤተሰቦችሽን ሁሉንም ትተሽ

መሄድሽ ነውና ወደ መኖሪያሽ

ከአማኑኤል ጋራ ባልሽን ይዘሽ

ተነሽ ሙሽራዬ ደርሷል ሰዓትሽ

ከድንግልም ጋራ ሚስትህን ይዘህ

ተነስ ወንድሜ ሆይ ደርሷል ሰዓትህ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening