✦
ጠቅላላ
•General
ንጽሕት ድንግል
Lyrics
ንጽሕት ድንግል ቡሩክት
የአምላክ እናት እመቤት
ልጆችሽ ሙሽሮች ሁለቱም አንድ ሆኑ
ተዋሃዱ ተጣመሩ በቅዱስ ቁርባኑ
ፍጹም መንፈሳዊ ልዩ ፍቅር
አንቺ ያለሽበት መልካም ትዳር
መሠረቱ ዛሬ ልጆችሽ
ቅድሰት ሆይ ባርኪያቸው ተነኝተሽ
ድንግል ጐጇቸውን ቀድሰሽ
እውነተኛ ፍቅር መሥርተሽ
በመካከላቸው ተነኝተሽ
ሁሉን አሰጪያቸው አማልደሽ
ሙሽሮቹም አምነው በምልጃሽ
እናታችን ባርኪን ነይ ሲሉሽ
ፈጥነሽ ድረሽና በሠርጋቸው
ነይ ተመላለሺ መሃላቸው
አንቺን ለሚወዱሽ ለሚያምኑሽ
የሕይወት አጣፋጭ ቅመም ነሽ
ሙሽሮቹም ዛሬ ይጠሩሻል
የጐጇችን ፋና ነይ ይሉሻል
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.