✦
ጠቅላላ
•General
የቤታችን እራስ
Lyrics
የቤታችን እራስ ልጅሽ ነው
አማላጅነትሽ የሚያድነን ነው /2/
እመብርሃን /2/ ሰላም አንቺ እኮ ነሽ እመቤታችን
ምን አለንና እኛ በጓዳችን
የጎደለ ነው ያለው ማድጋችን
ነይ ከልጅሽ ጋር እንድትሞይልን
ድንግል እመቤታችን
ያለን ውሃ ነው ከባዶ ጋን ጋራ
የጓዳውም ወይን ብዙም አላፈራ
የድሃ ጎጇችን እንዲባረክልን
ድንግል አሳስቢልን
በሰራፕታ ምድር ታምራት ያረገ
በኤልያስ አድሮ ሕዝቡን የባረከ
ዛሬም እርሱ ነው የቤቱ ሰላም
አምላክ መድሃኔዓለም
ጭንቀትን አይተሽ የልብን ሃዘን
ታሳስቢያለሽ እንዲጎበኘን
እኛም አንቺን ጠርተን ከእፍረት ድነናል
ድንግል ክብር ይገባሻል
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.