✦
ጠቅላላ
•General
ድንቅ ነው በጣም
Lyrics
ድንቅ ነው በጣም ድንቅ ነው /2/ በጣም
በሠርጋችን እለት ተገኘ መድሃኒዓለም
በሠርጋችን እለት ተገኘች ድንግል ማርያም
በቃልህ ተመርተው ለዚህ ቀን በቅተዋል
በፊትህ ጋብቻን ይኸው ፈጽመዋል
በፈሰሰው ደምህ ህብረት መስርተዋል
በሥጋም በነፍስም /2/ የአንተነን ብለዋል
የአዳምን አንድ አጥንት ከጎኑ ወስደህ
አጋር እንድትሆነው ሔዋንን ሰጠህ
ሁለቱንም ባርከህ እንደፈጠርካቸው
ዛሬም ለሙሽሮች /2/ ሰላምን ስጣቸው
ጌታ ሆይ ፍቅርህን በቃልህ መሰረት
አንድ ሆነዋልና በዚች ቅድስት ዕለት
እርሱንም እርሷንም ባርከህ ቀድሳቸው
ዘላለማዊ ክብር /2/ ጸጋህን ስጣቸው
የዲያብሎስ ተንኰል እንዳያጠምዳቸው
እስከመጨረሻው ጋሻ ሁንላቸው
ከቅዱስ ቁርባኑ ሁለቱም ሳይርቁ
ጽናቱን ስጣቸው /2/ አብረውኢ እንዲዘልቁ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.