ጠቅላላ

General

አምሮ ሲያበራ

Lyrics

አምሮ ሲያበራ ኑ ተመልከቱ /2/

በእግዚአብሔር ክብር ሲመላ ቤቱ /2/

ማነው የገባው በዚህ ጣራ ስር

ለሙሽሮች ደስታ ሊያበስር

ቤቱ ተመላ ሰላም ፍሥሐ

እናቅርብለት ምስጋና አምሀ

በአብርሃም ቤት የተገለጠው

በአልዓዛር ቤት እራት የበላው

ከእናቱ ጋራ ገባ ከቤቱ

ቤተ ዘመዱ ኑ ተደሰቱ

የእኛ ሙሽራ ደስ ይበልህ

ታላቅ እንግዳ ገብቷል ቤትህ

ሙሽራችን ሆይ ደስ ይበልሽ

የሰማይ ንግሥት ጎበኘችሽ

ለእድምተኞቹ መልካም ወይን አለን

የቃናው ጌታ የጠመቀልን

አናፍርም እኛ እንግዳ ጠርተን

አምላክ ከእኛ ጋር ስለሆነልን

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening