ጠቅላላ

General

ወንድና ሴት

Lyrics

ወንድና ሴት አርጎ እንደፈጠራቸው

ኋላም ለኑሯቸው ጋብቻን ሰጣቸው

አንዴ ከተጋቡ አንድ ሥጋ ናቸው

ከእንግዲህ ወደፊት ይጸናል ፍቅራቸው

ደስ ይበለን ሙሽሪት ሙሽራው /2/

አንድ አካል ሆነዋል አምላክ አጣምሯቸው

በምንም ምክንያት ምንም አይለያቸው

በጣም ይወዳታል በክብርት ሚስቱን

ስለሷ አሳልፎ ይሰጣል ነፍሱን

ለአብርሃም ለሣራ እንደሰጠ ትዳር

ለእናንተም ይለግስ የዘለዓለም ፍቅር

አንቺም እንደ ሣራ እርሱም እንደ አብርሃም

ተፋቅራችሁ ኑሩ እስከ ዘለዓለም

ለዚህ ላበቃችሁ ለቸሩ አምላካችን

ምሥጋና ይድረሰው ዛሬ ከሁላችን

በሉ ደህና ግቡ ወደ አዲስ ጎጆአችሁ

አምላክ በጥበቡ ፍቅርን ያብዛላችሁ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening