✦
ጠቅላላ
•General
ንሴብሆ
Lyrics
ንሴብሆ ለሥላሴ /2/
ክብር ተመስገን አምላከ ሙሴ /2/
የእኛ አማላጅ እናታችን
ነይ ነይ ወደእኛ እመቤታችን
ፈጥነሽ ተገኚ በመሃላችን
ና ወደእና ሚካኤል /2/
መልአከ ምክሩ ለልዑል
ከእግራችን ይውደቅ ሳጥናኤል
ና ወደእኛ ገብርኤል /2/
ከእሳቱ አውጣን ከነበልባል
በክንፍህ ጥላ እንጠለል
ና ወደእኛ ዑራኤል /2/
እንደ ቅዱስ ዕዝራ ሱቱኤል
ጥበብን ስጠን ማስተዋል
ና ወሰእኛ በፈረስ
የልዳው ፀሐይ ጊዮርጊስ
ገድልህን ሰምተን እንፈወስ
ና ወደእኛ ተክለሃይማኖት /2/
ይጠበቀን የአንተ ጸሎት
ጸንተን እንድንቆም በሃይማኖት /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.