✦
ጠቅላላ
•General
ዕፀ መስቀል
Lyrics
እንድንመስለው ጌታችንን /2/
እንሸከመው ዕፀ መስቀሉን /2/
እንድንሸከም ዕፀ መስቀሉን /2/
ሰውነታችንን ማንጸት አለብን /2/
እፀ መስቀል የክብር መውረሻ
ሰይጣን ድል መንሻ /2/
የክብር ባለቤት፣ እፀ መስቀል
የተሰዋበት እፀ መስቀል
የእኛ መድኃኒት፣ እፀ መስቀሉ ነው
ፍፁም አክብራችሁ፣ እንደ ዕሌኒ ንግስት
ሁላችሁ ገስግሱ፣ መስቀሉን ይዛችሁ
ያለ ኃይለ መስቀል፣ የሰላም አርማችን
ሰይጣን ጠላታችን፣ ሊሸነፍ አይችልም
እሳተ መለኮት፣ ያላቃጠለው
ሰይጣንን የሚያነድ፣ እፀ መስቀል ነው
እንደተባረከው፣ ቆስጠንጢኖስ ንጉሥ
ወደ እውነት እንገስግስ፣ በመስቀል ብርሃን
የተዋህዶ ልጆች፣ ገስግሱ በተስፋ
ጠላት እንዲጠፋ፣ እፀ መስቀል ያዙ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.