ጠቅላላ

General

መስቀል አበባ

Lyrics

መስቀል አበባ ነህ ውብ አበባ

ዓደይ አበባ ነሽ ውብ አበባ

መስቀል አበባ ተቀብሮ ሲኖር ፤ ዓደይ አበባ ፤ ስነ ስቅለቱ

መስቀል አበባ እሌኒ አገኘች ፤ ዓደይ አበባ ፤ ደገኛይቱ

መስቀል አበባ ጥራጊ ሞልተው ፤ ዓደይ አበባ ፤ አይሁድ በክፋት

መስቀል አበባ ጢሱ ሰገደ ፤ ዓደይ አበባ ፤ መስቀል ካለበት

መስቀል አበባ ወንዙ ጅረቱ ፤ ዓደይ አበባ ፤ ሸለቆ ዱሩ

መስቀል አበባ አሸብርቀው ደምቀው ፤ ዓደይ አበባ ፤ ለአንተ መሰከሩ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening