ጠቅላላ

General

ደስ ይበለን

Lyrics

ደስ ይበለን እልል በሉ /2/

አልቀረም ተቀብሮ ተገኘ መስቀሉ /2/

በብርሃን መላት ዓለምን በሙሉ /2/

ምን ቢተባበሩ ምቀኞች ቢጥሩ /2/

ቅዱስ መስቀሉንም ሸሽገው ቢሰውሩ /2/

አልቻሉም ሊያጠፉት ምን ቢተባበሩ /2/

በተራራ ተሰውሮ ለዘመናት /2/

ተጥሎ በተንኮል ተደብቆ ከኖረበት /2/

ተገለጠ ዛሬ በደመራ እሳት /2/

ዕሌኒ ናት ይህን ምስጢር ያስገኘችው /2/

ደመራን በቦታው በጥበብ ያስቆመችው /2/

የተንኮልን ተራራ ያስቆፈረችው /2/

ታሪካዊ የክርስቶስ ሕያው መስቀል /2/

ተገለጠ ዛሬ በክብር በግሩም ኃይል /2/

ምንጊዜም ሲያበራ እንዲህ ይኖራል /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening