ጠቅላላ
•General
ኢዮሃ አበባዬ
ኢዮሃ አበባዬ መስከረም ጠባዬ /2/
መስከረም ሲጠባ በመስቀል ደመራ፣
አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
በኃጢአት ጨለማ ተውጠን ሳለን፣
የክርስቶስ መስቀል ብርሃን ሆነልን፣
መስቀሉን አምነን ተሳልመነዋል፣
በክብሩ ዙፋን እርሱ ባርኮናል፣
እንሰግድለታለን የፀጋ ስግደት፣
በእርሱ ላይ ስላለ ኃይለ መለኮት፣
ትእምርተ መስቀል ሆኖን ላመንነው፣
መስቀል የእኛ ጋሻ የዲያቢሎስ ድል መንሻ፣
የኢትዮጵያ መኩሪያ፣
በኢየሩሳሌም አይሁድ አብረው፣
ከመሬት ቀብረው መስሏቸው ነበር፣
ምድር የሚያስቀረው፣
በቀራንዮ ጎልጎታ ጠላታችን ድል ተመታ /2/
ንግሥቲቷ ዕሌኒ በጣም የታደለች፣
ደመራን አቁማ ፀሎት አቀረበች፣
መስቀል ተሸክሞ ብርሀን እያበራ፣
መስቀለ ክርስቶስ፣
የመስቀሉ ፍቅር በእኛ ላይ ይደር /2/
ወዴት ነው እያለች ሲፈልግ ሰንብቶ፣
በዕጣን ጢስ ተማርታ መስቀሉን አገኘች፣
ቆስጠንጢኖስ ድል መታ /2/
ነገር ግን መስቀል፣ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ፣
ግሸን ላይ አገኘው፣
ተቀብሮ አልቀረ፣
በአምባሰል ተራራ፣ ተራራ አፍርሶ፣
ግማደ መስቀሉ፣ ጠላት አሳፈረ፣
አርፏል ከዚያ ስፍራ፣
መስቀል ሲወጣ፣ ቀና ጎባጣ፣
መስቀል መስቀላችን የክርስቲያን ኃይላችን /2/
የመስቀል ለታ፣ የደመራው፣
ድውይ ሲፈወስ፣ አንካሳ መጣ፣
ሙታን ተነሱ፣ ይመስገን ጌታ፣
ኢትዮጵያውያን፣ ተደስተው፣
በሀገር ልብሳቸው አምረው ደምቀው፣
ብርሃን ወጣ ከመስቀሉ ክርስቲያኖች እልል በሉ /2/
መስቀል መከታ ይሁን ጋሻችን፣ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ፣
በአደባባዩ፣ ተሰብስበው፣ ይዘምራሉ፣
መስቀል በኢትዮጵያ ሲያበራ /2/
የመስቀሉ ደመራ፣
እንዳይደፈር፣ ዳር ድንበራችን፣
ኢትዮጵያ ኑሪ ፣ በእምነት ፀንተሽ፣
ጌታ በመስቀል ፣ የባረከሽ፣
እንደ ፀሐይ ጮራ /2/ መስቀሉ አበራ።
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.