ጠቅላላ

General

የዓለም በደል

Lyrics

የዓለምን በደል የሰውን ግፍ አይቶ

ዘጠና ዘጠኙን መላእክቱን ትቶ

ጽድቅን ለመፈጸም በደልን አጥፍቶ

የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ

አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለእኛ /2/

የሰማዮች ሰማይ የማይችለው ንጉሥ

ተወለዶ ሲጠመቅ እኛን ለመቀደስ

ተራሮች ደንግጠው ዘለሉ እንደፈረስ

ባሕር ተጨነቀች ጠበባት መሬቱ

ዮርዳኖስ ሸሸ አልቆመም ከፊቱ

እንደተናገረው ዳዊት በትንቢቱ

እንደምናነበው በወንጌል ተጽፎ

መንፈስ ቅዱስ ታየ በራሱ ላይ አርፎ

በርግብ ምሳሌ ክንፋን አሰይፎ

ልጁ በዮርዳኖስ ጽድቅን ሲመሠርት

መጣ በደመና ሰማያዊ አባት

እየመሰከረ የልጁን ጌትነት

ባሕር ስትጨነቅ ተራራው ሲጨፍር

ሰማዩ ሲከፈት ደመናው ሲናገር

ዓለም በዛሬው ቀን አየች ይህን ምሥጢር

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening