ጠቅላላ

General

ግነዩ ለእግዚአብሔር

Lyrics

ግነዩ ለእግዚአብሔር እስመ ሔር /2/

እስመ ለዓለም ምሕረቱ እስመ ለዓለም /4/

እናመስግንሽ የአምላክ እናት በዝማሬ /2/

የዓለም ቤዛ ነውና የማኅፀንሽ ፍሬ /4/

ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከአንቺ ተወልዶ /2/

መለኮት ወረደ ዮርዳኖስ እኛን ለመቀደስ /4/

በድንግልና የወለድሽው ክርስቶስ /2/

የድኩማኖች ብርታት ነው የሕሙማን ፈውስ /4/

በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ እዳችንን ፋቀ /2/

በቸርነቱ ጠበቀን ከበደል አራቀን /4/

ስምሽን የጠራ ዝክርሽንም የዘከረ /2/

በመንግሥተ ሰማይ ይኖራል እንደተከበረ /4/

ብርሃነ መለኮት ያደረብሽ አዳራሽ /2/

ቅድስት ቅዱሳን ማርያም ድንግል አንቺ ነሽ /4/

እመቤታችን እናታችን ማርያም /2/

የተማጸነሽ ይድናል ለዘለዓለም /4/

ድንግልናሽ ሳይለወጥ ወልድን የወለድሽ /2/

የጌታችን እናት ማርያም ድንግል አንቺ ነሽ

የጌታችን እናት ማርያም ንጽሕት አንቺ ነሽ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening