✦
ጠቅላላ
•General
አዳምን ያልተወው
Lyrics
አዳምን ያልተወው እንደተሰደደ /4/
እሰይ የምስራች ዛሬ ተወለደ /4/
አዳምን ያልተወው እንደተጨነቀ /4/
እሰይ የምስራች ዛሬ ተጠመቀ /4/
አዳምን ሊጠራ የመጣው ሙሽራ /4/
በገሊላ አውራጃ ለሰርግ ተጠራ /4/
ሰርግ ቤት እንዳለ በክብር ተቀምጦ /4/
የወይን ጠጅ ሆነ ውኃው ተለውጦ /4/
በገሊላ አውራጃ ይህን ተዓምር ሠራ /4/
እጅግ ያስደንቃል የአምላካችን ሥራ /4/
ጌታችን አንድ ቀን ያደረገው ተዓምር /4/
ሲያስደንቅ ይኖራል ይህን ሁሉ ፍጡር /4/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.