✦
ጠቅላላ
•General
ዮሐንሰኒ
Lyrics
ዮሐንስኒ ያጠምቅ /2/
በሔኖን /5/ በማዕዶተ ዮርዳኖስ
ዮሐንስ ሲያስተምር ያጠምቅ
በጫካ በሜዳ ያጠምቅ
ግምል ፀጉር ለብሶ ያጠምቅ
ሆኖ ምድረ በዳ ያጠምቅ
አምላኩን የሚወድ ያጠምቅ
ብዙ ሰው እያለ ያጠምቅ
ጌታውን ለማጥመቅ ያጠምቅ
ዮሐንስ ታደለ ያጠምቅ
ኮረብታው ይደልደል ያጠምቅ
ጠማማውም ይቅና ያጠምቅ
እያለ ሰበከ ያጠምቅ
ሥርዓቱ ነውና ያጠምቅ
ከኃጢያት ተለዩ ያጠምቅ
በውሃ ተጠመቁ ያጠምቅ
መንግስተ ሰማያት ያጠምቅ
እንዳለች እወቁ ያጠምቅ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.