ጠቅላላ

General

ጥምቀተ ባሕር

Lyrics

ጥምቀተ ባሕር ዮርዳኖስ ነያ /2/ ሀሌሉያ /4/

ጌታችን ሲጠመቅ ባሕር ምን አለች

አልችለውም ብላ ወደፊት ሸሸች

ብርሃነ መለኮት በወንዙ ሲሞላ

ዮርዳኖስም ሸሸ ቀረ ወደኋላ

አብ ነበር የመጣው ደመናውን ጭኖ

መንፈስ ቅዱስ ታየ በርግብ አምሳል ሆኖ

ለልጁ ምስክር ሊሰጥ ፈለገና

አብም ተነገረ ሆኖ በደመና

ቃሉን በመጣ ጊዜ ልሆን

ጌታችን ሲጠመቅ በ30 ዓመት

ባህር ኮበለለች ግዑዟ ፍጥረት

ሰማይ ተከፈተ ሆነልን ጸአዳ

እልል በይ ዮርዳኖስ የጽድቅ መገኛ

የሕይወት መሠላል ድኅነታችን ለእኛ

ቀላያት አብርህት ብዙዎች እያሉ

እንደምን ተመረጥሽ ዮርዳኖስ ከሁሉ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening