✦
ጠቅላላ
•General
የሰላሙ መሪ
Lyrics
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ /2/
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለእኛ /2/
ወለደን በጥምቀት በመንፈስ ዳግመኛ /2/
የንጉሦች ንጉሥ የጻድቃን እረኛ /2/
ለመልካሙ ሥራ በእምነት እንበርታ /2/
ከሰይጣን ባርነት ነጻ አወጣን ጌታ /2/
የዛሬው ጥምቀቱ ተነግሮ በአዋጅ /2/
ነጻነት አገኘን በእግዚአብሔር አብ ልጅ /2/
እግዚአብሔር አብ ላከ አንድያ ልጁን /2/
እርሱ ወዷልና እንዲሁ ዓለሙን /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.